
ዩኒቨርሲቲው ልሳነ ብዙ አለም አቀፍ የሰነድ ንብረት ማዕከል ገንብቷል። የቤተ መፃህፍቱ የወረቀት ሰነዶች ስብስብ በ107 ቋንቋዎች የተጻፉ ሲሆን ወደ 1.6 ሚሊዮን የሚጠጉ ናቸው። ከ1.41 ሚሊዮን በላይ የኤሌክትሮኒክስ መጽሃፎች፣ 873 የወረቀት ጋዜጦች እና ወቅታዊ ጽሑፎች እና 103 የመረጃ ቋቶች አለው። ቋንቋ፣ ስነ-ጽሁፍ እና ባህልን እንደ ዋና ሰነዶች የያዘ ክምችት ነው።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የትምህርት መሥኮችን በማሳደግ፣ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በዲፕሎማሲ፣ በሕግ ፣ በዜና፣ በአስተዳደር፣ በአገራዊ እና በክልላዊ ጥናቶች ዙሪያ ያሉ ጽሑፎችን ቀስ በቀስ የሚሰበሰቡበትን ሥርዓት ፈጥሮ እያሰባሰበ ይገኛል። ዩኒቨርሲቲው ተደራሽ፣ የተሳለጠ፣ ብቁ፣ በአዳዲስ ፈጠራዎች የታገዘ እና የተቀናጀ የመረጃ መዋቅር በመገንባት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅዎችን መጠቀሙን ቀጥሏል፡፡ በተጨማሪም የሶፍትዌር መስኮችን በማዳበር እንደ የባለ ብዙ ቋንቋ ኦፊሴላዊ ድረ-ገጽ፣ ስማርት የምዝገባ መድረክ፣ የመረጃ ማዕከል እና የመስመር ላይ የማስተማር እና የማስተማር ግብአት መድረኮችን አዘጋጅቷል። ፈጠራን እና እድገትን ለማመቻቸት አስተውሎታዊ የማስተማሪያ አካባቢዎችን እና ለመምህራን ሥራ የሚያግዙ ዘመናዊ የማስተማሪያ መሳሪያዎችን እና ቤተ ሙከራዎችን በመገንባት አስደናቂ ውጤት አስመዝግቧል። BFSU የትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንን ልማት በሰው ሰራሽ አስተውሎት ለማሳደግ ለተቀረፀው የሙከራ ፕሮጀክት ከተመረጡ የመጀመሪያዎቹ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ሆኗል፡፡ የቋንቋን አጀማመር፣ አሁን የደረሰበትን ደረጃና ባህል ለማሳየት የሚያስችል ዘመናዊ የዓለም ቋንቋዎች ቤተ መዘክር እንዲሁም የBFSUን ታሪክ ሙሉ ለሙሉ የሚዘክር አዲስ የታሪክ ሙዚየም አቋቁሞ ለተጠቃሚዎች ክፍት አድርጓል፡፡

ቤተ መፃህፍቱ ባለ ስድስት ወለል ሆኖ በአጠቃላይ 23,000 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ፎቅ ነው። በውስጡም ከ2,200 በላይ የንባብ መቀመጫዎችን፣18 የጥናት ክፍሎችን፣ የአካዳሚክ ትምህርት አዳራሾችን፣ የአካዳሚክ ሴሚናር አዳራሾችን፣ የስልጠና ክፍሎችን፣ ወዘተ. የያዘ ነው፡፡ በተጨማሪም የኤግዚቢሽን አዳራሾችን፣ የመምህራን መጽሃፍ ቤቶችን፣ የተማሪዎች የመጽሃፍ ካፌን፣ የሚያስደምሙ የቋንቋ እና የባህል ማዕከላትን እና ሌሎች የባህል እና የመዝናኛ ቦታዎችን ይዟል።
ቤተ መፃህፍቱ በሙሉ በገመድ አልባ የመረጃ መረብ የተሸፈነ ሲሆን የ24 ሰዓት የግል የሚከናወን የመጽሐፍ መመለሻ አገልግሎት መስኮት አለው። የተለያዩ የግል አገልግሎት መሳሪያዎችን ማለትም የግል ፍቶ ኮፒ ፣ ማተም፣ ስካን ማድረግ የሚያስችሉ፣ መፅሃፍ መበደር እና መመለስ፣ ኤሌክትሮኒካዊ ዳሰሳ፣ ኤሌክትሮኒካዊ ጋዜጣ ንባብ እና የመሳሰሉትን አገልግሎቶችን የማንም እገዛ ሳያስፈልግ ማግኘት የሚያስችል ሆኖ የተደራጀ ነው፡፡ በተጨማሪም የኤሌክትሮኒክስ የማንበቢያ ቦታ፣ የመልቲሚዲያ የመማሪያ ቦታ እና በሁሉም ቦታ የሚታይ የመረጃ ማስላለፊያ ስርዓት አለው።

የBFSU ቤተ መፃህፍት "የውጭ፣ የተለዬ፣ ትክክለኛ እና ሁሉን አቀፍ" የሚለውን የዩኒቨርሲቲውን የትምህርት ፍልስፍና ያከብራል፡፡ ከሰዎች ተኮር መርሃ ግብር እና ከእውቀት ከኢኮኖሚ እና ከዲጂታል ልማት ፈጣን እንቅስቃሴ ጋር የሚስማማ ነው። ለአንባቢዎች በበለጸጉ የመሰብሰቢያ ግብዓቶች፣ ምቹ የመማሪያ አካባቢ፣ ሰብአዊነት የተላበሰ የአገልግሎት ጽንሰ-ሀሳብ እና በከፍተኛ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት የተሟላ የመረጃ አገልግሎቶችን እና አካዳሚያዊ ድጋፎችን
ይሰጣል። በተመሳሳይ የውጭ ቋንቋ አካዳሚያዊ እና የተለዩ ሀብቶችን ለማከማቸት ቁርጠኝነት ያለው ነው፡፡ ለዚህም በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እና በመካከላቸው ያሉ በርካታ ባህሎችን ለማዋሃድ የሚያስችል የመረጃ ማዕከል እና የባህል ልውውጥ ማዕከል በመሆን እያገለገለ ይገኛል፡፡