ዋናኛ ገጽ (ወደ መነሻ ገጽ ይመለሱ > ስለ ቤጂንግ ፎሪየን ስተዲስ ዩኒቨርሲቲ > ማስተዋወቂያ
>ማስተዋወቂያ
>የዩኒቨርሲቲው መሪ ቃልና ዓርማ
>የጊዜው አመራር
>ቁልፍ ዕውነታዎችና መረጃዎች
>የዩኒቨርሲቲው ገፅታ
>በዚህ ሊያገኙን ይችላሉ

ማስተዋወቂያ

ቤጂንግ ፎሪየን ስተዲስ ዩኒቨርሲቲ ወይም BFSU ቤጂንግ ምዕራብ ሶስተኛ ቀለበት መንገድ ሰሜን፣ ሃይዲያን አውራጃ የሚገኝ ሲሆን በትምህርት ሚኒስቴር አስተዳደር ስር ካሉ ተዋቂ የቻይና ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከቻይና የመጀመሪያዎቹ የ"211 ፕሮጀክት" ከታቀፉ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የተካተተ፣ ከ"985ቱ ጠቃሚ የዲሲፕሊን ፈጠራ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ሆነ እና መጀመሪያ ቡድን"ድርብ አንደኛ-ደረጃ" ከወጡ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንደኛው ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው እ... 1941 በቻይና ህዝብፀረ-ጃፓን ወታደራዊ እና የፖለቲካ ኮሌጅ ሦስተኛ ቅርንጫፍ ውስጥ የሩሲያ ቋንቋ ማስተማሪያ ኮሌጅ በመሆን ተቋቋመ በኋላ በቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ቀጥተኛ አመራር የማዕከላዊ ወታደራዊ ኮሚሽን የውጭ ቋንቋዎች ትምህርት ቤት ተባለ። የቻይና ህዝብ ሪፐብሊክ ከተመሰረተ በኋላ ትምህርት ቤቱ የሚተዳደረው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነበር፡፡ ... 1954 የቤጂንግ የውጭ ቋንቋዎች ተቋም ተብሎተሰየመ ሲሆን 1959 ከቤጂንግ የሩሲያ ቋንቋ ተቋም ጋር ተቀላቀለ። 1980 ጀምሮ ተቋሙ በቀጥታ የሚተዳደረው ትምህርት ሚኒስቴር ነው። ... 1994 ደግሞ አሁን የሚጠራበትን ቤጂንግ ፎሪየን ስተዲስ ዩኒቨርሲቲ የሚለውን ስያሜ አገኘ።

ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ጊዜ 101 የውጭ ቋንቋዎችን ያስተምራል። በቻይና ውስጥ ትምህርት ሚኒስቴር ልዩ የማስተማር መርሃ ግብሮች ውስጥ ብዙ ተናጋሪ ሌላቸው የአውሮፓ፣ የእስያ እና የአፍሪካ ቋንቋዎችን በማስተማር የመጀመሪያው ዩኒቨርሲቲም በመሆን ቀጥሏል፡፡ BFSUውጪ ቋንቋዎች እና ሥነ ጽሑፍን በማስተማር የላቀ ደረጃ ላይ የደረሰ ብቻ ሳይሆን እንደ ሂዩማኒቲስ ህግ፣ ኢኮኖሚክስ፣ አስተዳደር እና ሥነ ትምህርት ባሉ ዘርፎች ፕሮግራሞችን በመክፈት በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡ BFSU በአሁኑ ሰዓት የቻይናን ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል ከቻይና ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩትን 183 ሀገራት ኦፊሴላዊ ቋንቋዎችን ያስተምራል፡፡ እነዚህም (በጊዜ ቅደም ተከተል) ራሽያኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ጀርመንኛ፣ ስፓኒሽ፣ ፖላንድኛ፣ ቼክ፣ ሩማኒያኛ፣ ጃፓንኛ፣ አረብኛ፣ ካምቦዲያኛ፣ ላኦኛ፣ ሲንሃሌዝ፣ ማሌይኛ፣ ስዊድንኛ፣ ፖርቱጋልኛ፣ ሃንጋሪኛ፣ አልባኒያኛ፣ ቡልጋሪያኛ፣ ስዋሂሊኝ፣ በርማኛ፣ ኢንዶኔዥያኛ፣ ጣሊያንኛ፣ ክሮኤሺያኛ፣ ሰርቢያኛ፣ ሃውሳኛ፣ ቬትናምኛ፣ ታይሎቫክኛ፣ ቱርክኛ፣ ኮሪያኛ፣ ኖርዌጂያን፣ አይስላንድኛ፣ ፊኒሽኛ፣ ዳኒሽኛ፣ ግሪክኛ፣ ፊሊፒንኛ፣ ሂንዲኛ፣ ኡርዱኛ፣ ዕብራይስጥኛ፣ ፋርስኛ፣ ስሎቪኛ፣ ኢስቶኒያኛ፣ ላትቪያኛ፣ ሊቱዌኒያኛ፣ አይሪሽኛ፣ ማልቴስኛ፣ ቤንጋሊኛ፣ ካዛክኛ፣ ኡዝቤክኛ፣ ላቲንኛ፣ ዙሉኛ፣ ኪርጊዝኛ፣ ፓሽቶኛ፣ ሳንስክሪትኛ፣ ፓሊኛ፣ አማርኛ፣ ኔፓልኛ፣ ሶማሊኛ፣ ታሚልኛ፣ ቱርክሜንኛ፣ ካታላኛ፣ ዮሩባኛ፣ ሞንጎሊያኛ፣ ማላሲያኛ መቄዶኒያኛ፣ ታጂክኛ፣ ፅዋናኛ፣ ንዴቤሌኛ፣ ኮሞሪያንኛ፣ ክሪኦልኛ፣ ሾናኛ፣ ትግሪኛ፣ ቤላሩስኛ፣ ማኦሪኛ፣ ቶንጋንኛ፣ ሳሞአንኛ፣ ኩርዲሽኛ፣ ቢስላማኛ፣ ዳሪኛ፣ ቴቱምኛ፣ ዲቪሂኛ፣ ፊጂያንኛ፣ ኩክ ደሴቶች ማኦሪኛ፣ ኪሩንዲኛ፣ ሉክሰምበርጊኛ፣ ኪንያርዋንዳኛ፣ ኒዌያንኛ፣ ቶክ ፒሶማኛ፣ ቼዋኛ፣ ሴሶቶኛ፣ ሳንጎኛ፣ታማዚትኛ፣ ጃቫኛ እና ፑንጃቢኛ የተሰኙትን ቋንቋዎች በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡

BFSU በቅርብ ዓመታት ውስጥ አዲስ የተቋቋሙትን ጨምሮ በማስተማር እና በምርምር መሥክ የተሰማሩ ትምህርት ቤቶች፣ የትምህርት ክፍሎች እና ማዕከሎች አሉት። እነሱም በአገር ውስጥ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው የማስተማሪያ ቁሳቁስ ማምረቻ ክፍል፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ትምህርት ቤት፣ የድህረ ምረቃ ትምህርት ቤት፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና የቋንቋዎች ቤተ ሙከራ (BFSU•AI) እና ጥናትና ምርምር ለአገር-ተኮር የትርጉም እና የትርጓሜ አቅም ያካትታሉ። በተጨማሪም ቀደም ሲል አንድ ላይ የነበረው የእስያ እና የአፍሪካ ጥናቶች ትምህርት ቤት በሁለት ራሳቸውን የቻሉ ትምህርት ቤቶች ማለትም የእስያ ጥናቶች ትምህርት ቤት እና የአፍሪካ ጥናቶች ትምህርት ቤት በመሰኘት እንደገና ተዋቅረዋል ዩኒቨርሲቲው ዓለም አቀፋዊ ቋንቋዎች አንፃር ዓለም አቀፋዊ ባህል እና አስተዳደር ቀዳሚ ስትራቴጂዎቹ በመሆናቸው ዓለም አቀፍ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲዎች ጥምረት፣ አለም አቅፍ የሀገርና አካባቢ ጥናቶች ጥምረት እና የቻይና የሀገርና አካባቢ ጥናቶች ጥምረት የተሰኙ ተቋማትን መሥርቶ እየሠራ ይገኛል

ዩኒቨርሲቲው የትምህርት ሚኒስቴር ሰብአዊነት እና ማህበራዊ ሳይንስ ቁልፍ የምርምር ተቋም ጨምሮ 54 ብሔራዊ እና የክልል የምርምር ተቋማት አሉት፡፡ እነሱም የቻይና የውጭ ቋንቋ እና የትምህርት ምርምር ማዕከልየትምህርት ሚኒስቴር የምህንድስና ምርምር ማዕከል ልማት እና የግንባታ ፕሮጀክት፣ ቁልፍአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና የቋንቋ ላቦራቶሪየብሔራዊ ቋንቋ ኮሚቴ የምርምር ማዕከል፣ የብሔራዊ ቋንቋ ችሎታ ልማት ምርምር ማዕከልየብሔራዊ የመማሪያ መጽሀፍ ልማት ቁልፍ የምርምር ተቋም፣ዩኒቨርሲቲ፣መካከለኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የውጭ ቋንቋ የመማሪያ መጽሀፍ ምርምር ተቋም፣ የትምህርት ሚኒስቴር ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ አገሮች እና ክልሎች፣ ዓለም አቀፍ ኮሙኒኬሽን ጥምር ምርምር ኢንስቲትዩት ተሻጋሪ የፈጠራ መድረክ፣ ክልላዊ እና ዓለም አቀፋዊ የአስተዳደር ተቋም፣ አራቱ የትምህርት ሚኒስቴር ክልላዊ እና ሀገራዊ የምርምር ተቋማት የሆኑት እነሱም፡- የመካከለኛው እና የምስራቅ አውሮፓ የምርምር ማዕከል፣ የጃፓን የምርምር ማዕከል፣ የብሪቲሽ የምርምር ማዕከል እና የካናዳ የምርምር ማዕከል ናቸው፡፡ እንዲሁም 37 የትምህርት ሚኒስቴር ሀገራዊና እና ክልላዊ የምርምር ምዝገባ ማዕከላት፣ 3 የትምህርት ሚኒስቴር ቻይና ከውጭ ሀገራት ጋር ያደረገቻቸው የሰብአዊነት ትብብሮች የምርምር ማዕከላት የሆኑት ቻይና-ኢንዶኔዥያ የሰብአዊነት ትብብር የምርምር ማዕከል፣ ቻይና-ፈረንሳይ የሰብአዊነት ትብብር የምርምር ማዕከል፣ ቻይና-ጀርመን የሰብአዊነት ትብብር ምርምር ማዕከከል ይገኛሉ፡፡ ዩኒቨርሲቲው በተጨማሪም የቤጂንግ ቁልፍ የምርምር፣ የፍልስፍና እናማህበራዊ ሳይንስ ተቋም እና የቤጂንግትምህርት ህግ ምርምር ማዕከል ያለው ሲሆን የብሔራዊ ቋንቋ ማስፋፊያ ተቃማት የመጀመሪያው ቡድን እና የቤጂንግ ጂንፒንግ የሶሻሊዝም ፍልስፍና ከቻይንኛ ባህሪያት ምርምር ተቋም ጋር የመጀመሪያ ቡድን በመሆን ተመርጧል፡፡ እንዲሁም የቤጂንግ ዩኒቨርሲቲ የሶሻሊዝም ቲዎሪ ምርምር የትብብር ፈጠራ ማዕከል በመሆን ተሸልሟል።

BFSU አምስት የቻይና ማህበራዊ ሳይንሶች የመረጃ ማውጫ (Chinese Social Sciences Citation Index CSSCI) ምንጭ የሆኑ ጆርናሎችን ያትማል፡፡ እነዚህም የውጭ ቋንቋ ትምህርት እና ምርምር፣ የውጭ ሀገር ሥነ ጽሑፍ፣ ዓለም አቀፍ መድረክ፣ የውጭ ቋንቋ ትምህርት በቻይና እና ዓለም አቀፍ ሳይኖሎጂ ናቸው፡፡ በተጨማሪም ሩሲያኛ በቻይና የተሰኘ እንደ CSSCI ዓይነት ጆርናል አለው፡፡ እንዲሁም የጃፓን ጥናቶች እና የቋንቋ ፖሊሲ እና ዕቅድ ጆርናልን ጨምሮ በርካታ የCSSCI ምንጭ ተከታታይ ጆርናሎች እና ሌሎች ሰባት የቻይና አካዳሚክ ጆርናሎች እና በEmerging Sources Citation Index (ESCI) የሚጠቀሱ የተግባራዊ ሊንጉስቲክ ጆርናል፣ የዓለም ቋንቋዎች ጆርናል እና ትርጉምና ማህበረሰብ የተሰኙትን የመሳሰሉ ባለ ፈርጀ ብዙ ጥናቶችን የሚያካትቱ የእንግሊዝኛ ቋንቋ መተግበሪያ ጆርናሎች አሉት፡፡ በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው የውጭ ቋንቋ ትምህርት እና ምርምር ፕሬስ (FLTRP) የተሰኘ በቻይና ውስጥ ለውጭ ቋንቋ መጽሃፍቶች፣ ለድምጽ እና ምስል ምርቶች እና ለዲጂታል ምርቶች ህትመት ተመራጭ የሆነ ትል ማተሚያ ቤት የሚያስተዳድር ነው

BFSU 122 የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞችን ይሰጣል፣ 46 በዚህ ዩኒቨርሲቲ ብቻ የሚገኙ ናቸው። በተጨማሪም በሀገር አቀፍ ደረጃአንደኛ ደረጃነት የተመረጡ 54 የቅድመ ምረቃ መርሃ ግብሮች እና 18 በክፍለ ሀገር ደረጃ በአንደኛ ደረጃነት የተመረጡ የቅድመ ምረቃ መርሃ ግብሮች አሉት፡፡ በ2022 በብሔራዊ ደረጃ በተካሄደው የማስተማር ስኬት ውድድር የ"BFSU ሞዴልሁለገብቋንቋ ችሎታን በማዳበር" ዘርፍ አንደኛ በመውጣት ተሸላሚ ሆኗል፡፡

BFSU በብሔራዊ ደረጃ የትምህርት ልማትን ጨምሮ አራት ቁልፍ የትምህርት ፕሮግራሞችን እና በማዘጋጃ ቤት ደረጃ ሰባት ቁልፍ የትምህርት ፕሮግራሞችን ይሰጣል፡፡ እንዲሁም የውጭ ቋንቋዎች እና ሥነ ጽሑፍ፣ በአስተዳደር ሳይንስ እና ምህንድስና፣ የሀገር እና የአካባቢ ጥናቶች፣ በቻይና ቋንቋ እና ሥነ ጽሑፍ፣ በትምህርት እና የትርጉም ጥናቶች ዘርፍ በ3ኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ደረጃ አሰልጥኖ ያስመርቃል፡፡ በሁለተኛ ዲግሪ ደረጃም 12 ፕሮግራሞች ያሉት ሲሆን እነዚህም የውጪ ቋንቋዎችና ሥነ ፅሁፍ፣ በአስተዳደር ሳይንስ እና ምህንድስና፣ የቻይንኛ ቋንቋ ሥነ ጽሑፍ፣ የሀገር እና የአካባቢ ጥናቶች፣ የትምህርት ጥናቶች፣ የፖለቲካ ሳይንስ፣ የጋዜጠኝነት ጥናቶች፣ ሕግ፣ ተግባራዊ ኢኮኖሚክስ፣ የንግድ ሥራ አመራር፣ የማርክሲዝም ንድፈ ሐሳብ እና የዓለም ታሪክ ናቸው፡፡ በተጨማሪም ዘጠኝ የፕሮፌሽናል ማስተርስ ዲግሪዎችን ያሉ ሲሆን እነሱም ትርጉም እና መተርጎም፣ ቻይንኛን እንደ የውጭ ቋንቋ ማስተማር፣ ዓለም አቀፍ ንግድ፣ ፋይናንስ ፣ጋዜጠኝነት እና ኮሙኒኬሽን ህግ ሂሳብ የንግድ አስተዳደር እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ናቸው። በዩኒቨርሲቲው የሚሰጡት የውጭ ቋንቋዎች እና ጽሑፍ ፕሮግራሞች በብሔራዊ ደረጃ ድርብ አንደኛ ደረጃ ፕሮጀክት በተሰኘው ፕሮጀክት ውስጥ ተካተዋል፡፡ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው የውጭ ቋንቋ ፕሮግራሞቹ በቤጂንግ ውስጥ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የላቀ የትምህርት ፕሮግራም ሆነው ጸድቀዋል። በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ፕሮግራሞች ምዘና፣ የዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ደረጃ የትምህርት ፕሮግራም የሆነው የውጭ ቋንቋዎች እና ጽሁፍ በአገር አቀፍ ደረጃ አንደኛ ደረጃን አግኝተዋል። እንደ QS (Quacquarelli Symonds) የ2025 በዓለም ዩኒቨርሲቲዎች የደረጃ አሰጣጥ መስፈርት መሠረት (World University Rankings by Subject 2025) BFSU በሚያካሂደው የሥነ ቋንቋ ፕሮግራም በአለም አቀፍ ደረጃ 18ኛ ደረጃ በመውጣት በአገር ውስጥ ካሉ ተቋማት መካከል ከፍተኛ ቦታ ላይ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም በእንግሊዘኛ ቋንቋ እና ስነፅሁፍ በ98ኛ ደረጃ፣ በዘመናዊ ሥነ ቋንቋ ከ151ኛ-200ኛ አካባቢ እና በትምህርት በ251ኛ-300ኛ አካባቢ ውስጥ ይገኛል

የኒቨርሲቲው አካታችነትና እና ታጋሽነት ፣ መማር እና መለማመድበሚለው መሪ ቃል በመመራት በጎነትን የያጎለበቱ እና ለሚሠማሩበት መሥክ ብቁ የሆኑ ወጣቶችን በማፍራት አዲሱን ትውልድ የማብቃት መሰረታዊ ተግባሩን በስኬት እየተወጣ ይገል፡፡ በቻይና ውስጥ እና ከቻይና ውጭ ባሉ ሀገራት በዲፕሎማትነት፣ተርጓሚ/አስተርጓሚነት፣አስተማሪነት፣ስራ ፈጣሪነት፣ጋዜጠኝነት፣ በየህግ ባለሙያነት፣ በባንክ ባለሙያነት እና ሌሎችምስራ መሥኮች የተሠማሩ ጠንካራና ብቁ የቋንቋ ችሎታ ያላቸውን ከፍተኛ ባለሙያዎችን አፍርቷል። BFSU ካፈራቸው የቀድሞ ተማሪዎች መካከል 500 በላይ በአምባሳደርነት 3,000 በላይ ደግሞ በአማካሪነት ሰርተዋል፤ እየሠሩም ይገኛሉ ከዚህ የተነሳም ዩኒቨርሲቲው "የዲፕሎማቶች መፍለቂያ" በሚል ስም ለመታወቅ ችሏል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ወቅት 5,700 በላይ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች፣ 4,300 የድህረ ምረቃ ተማሪዎች እና 1,200 ዓለም አቀፍ ተማሪዎች አሉት። ... 2024 ዩኒቨርስቲው በቻይና ላሉ ዓለም አቀፍ ተማሪዎች በሚሰጠው ከፍተኛ ትምህርት ጥራት አንደኛ በመውጣት ዳግም እውቅና አግኝቷል።

BFSU ሥራን በአግባቡ የመምራትና የፈጠራ ክሎት ላላቸው አስተዳደር ሠራተኞች እና በሁሉም መስክ ብቃት ያላቸውን የመምህራን ቡድኑን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ የሚገኝ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ 1,200 በላይ የሙሉ ጊዜ ቻይናዊያን መምህራን እና ሰራተኞች እንዲሁም 57 አገሮች እና ክልሎች የመጡ ወደ 200 የሚጠጉ የውጭ መምህራን አሉት፡፡ የዩኒቨርሲቲው የፋኩልቲ አባላት የቻይና ህዝቦች ሪፐብሊክ የወዳጅነት ሜዳሊያ ተሸላሚዎች፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ ታዋቂ መምህራን እና በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላቸውን ባለሙያዎች የሚያካትቱ ናቸው። ከነዚህ መምህራን ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት የውጪ ሀገር ጥናት ልምድ ያላቸው ናቸው፡፡ የዩኒቨርሲቲያችን መምህራን ከየውጭ ቋንቋ ትምህርት ብሔራዊ የምርምር ማዕከል እና ለአለምአቀፍ አስተዳደር እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የተሰጥኦ ማሰልጠኛ ቡድን አባላት "የታዋቂው የጂኦፊዚክስ ሊቅ ሁአንግ ዳኒያን መንፈስ ወደፊት የሚያራምዱ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ቡድኖች" የሚል እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡

BFSU 80 በላይ ሀገሮች እና ክልሎች ከ300 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች እና የአካዳሚክ ተቋማት ጋር የትብብር እና በጋራ የመሥራት ስምምነቶችን ተፈራርሟል፡፡ ዋና ዋናዎቹን ለመጥቀስ የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ፣ የቺካጎ ዩኒቨርሲቲ፣ የናንያንግ የቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ የቶኪዮ ዩኒቨርሲቲ፣ የአውስትራሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ፣ የሶርቦኔ ዩኒቨርሲቲ፣ የሆንግ ኮንግ የቻይንኛ ዩኒቨርሲቲ፣ የማላያ ዩኒቨርሲቲ፣ የሞስኮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ፣ የሳኦ ፓውሎ ዩኒቨርሲቲ፣ የሃይደልበርግ ዩኒቨርሲቲ፣ የሜክሲኮ ብሄራዊ የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ እና የባርሴሎና ዩኒቨርስቲን ጨምሮ ከብዙ ታዋቂ የውጭ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የትብብር ፕሮግራሞችን ጀምሯል። ዩኒቨርሲቲው ከዚህ በተጨማሪ በ18 የእስያ፣ የአውሮፓ እና የአሜሪካ ሀገራት ውስጥ 23 የኮንፊሽየስ ኢንስቲትዩቶችን አቋቁሟል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 7ቱ የኮንፊሽየስ ኢንስቲትዩት የዓለም አቀፍ ሞዴሎች  ሲሆኑ ዩኒቨርሲቲያችን የኮንፊሸየስ ኢንስቲቲዩቶችን በውጪ ሀገራት በማቋቋም በአገር ውስጥ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ትልቁን ቁጥር የያዘ እንዲሆን አስችሎታል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በተለይ ለሥነ ጽሁፍ ባህሪያት የሚያገለግል የባለ ብዙ ቋንቋ አለም አቀፍ የመረጃ ማዕከል አቋቁሟል። BFSU ቤተ መፃህፍት 107 ቋንቋዎች በአብዛኛው በቋንቋ፣ ጽሁፍ እና ባህል ላይ የሚያተኩሩ ወደ 1.6 ሚሊዮን የሚጠጉ መጽሃፍት ክምችት ያለው ነው፡፡ ከዚህ ክምችት ውስጥ ከ1.41 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ኤሌክትሮኒክ መጽሐፍት፣ 873 የህትመት ጋዜጦች እና ወቅታዊ ጽሑፎች ሲሆኑ 103 የመረጃ ቋቶችም አሉት፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ፣ በአካዳሚክ የትምህርት ዘርፎች እድገት ምክንያት ቤተ መፃህፍቱ ስብስቦቹን በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚክስ፣ በዲፕሎማሲ፣ በህግ፣ በጋዜጠኝነት፣ በአስተዳደር እና በአገር እና አካባቢ ጥናት ዘርፎች የበለጠ አሳድጓል። ዩኒቨርሲቲው ተደራሽ፣ የተሳለጠ፣ ብቁ፣ በአዳዲስ ፈጠራዎች የታገዘ እና የተቀናጀ የመረጃ መዋቅር በመገንባት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅዎችን መጠቀሙን ቀጥሏል፡፡ በተጨማሪም የሶፍትዌር መስኮችን በማዳበር እንደ የባለ ብዙ ቋንቋ ኦፊሴላዊ ድረ-ገጽ፣ ስማርት የምዝገባ መድረክ፣ የመረጃ ማዕከል እና የመስመር ላይ የማስተማር እና የማስተማር ግብአት መድረኮችን አዘጋጅቷል። ፈጠራን እና እድገትን ለማመቻቸት አስተውሎታዊ የማስተማሪያ አካባቢዎችን እና ለመምህራን ሥራ የሚያግዙ ዘመናዊ የማስተማሪያ መሳሪያዎችን እና ቤተ ሙከራዎችን በመገንባት አስደናቂ ውጤት አስመዝግቧል። ዩኒቨርሲቲው በትምህርት ሚኒስቴር ሰው ሰራሽ አስተውሎት AI የታገዘ የመምህራን ልማት ተነሳሽነት ፕሮጀክት የመጀመሪያው ዙር ቡድን ውስጥ ፓይለት ዩኒቨርሲቲ በመሆን ተመርጧል። በተጨማሪም የዓለም ቋንቋዎች ቤተ መዘክር እና አዲስ የዩኒቨርሲቲውን ታሪክ የሚያመለክት ቤተ መዘክር ገንብቶ ለጎብኚዎች ክፍት አድርጓል፡፡ በዚህም የቋንቋ እና ባህላዊ መሠረቶችን በመገንባት በብዙ መልኩ ሁለንተናዊ የእድገት መንገድ ላይ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

በአሁኑ ጊዜ BFSU ራሱን በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ፣ ልዩከፍተኛ ደረጃ እና ሁሉን አቀፍ ደረጃ ያለው በዓለም የውጭ ቋንቋዎች ዩኒቨርሲቲ ለማድረግ ባለው ርዕይ መሠረት ተሰጥዖኣዊ ስልጠናን በማጠናከር፣ የአካዳሚክ ብቃትን በማስፋፋት እና ዓለም አቀፍ ዕውቅናዉን ለመገንባት ተግቶ በመሥራት ላይ ይገኛል። ዩኒቨርሲቲያችን ቻይናን ከሌላው ዓለም ጋር በቋንቋዎች የማገናኘት እናሁሉንም ህዝቦች እውነትን እና ፍትህን የመደገፍ ተልዕኮውን ለማሳካት ዓለም አቀፋዊ እይታ እና ሙያዊ አቅሙን ተመርኩዞ በርካታ ተሰጥዖዎችንና ችሎታዎችን ለማዳበር በሀገር ፍቅር ስሜት ይተጋል። እነዚህ ጥረቶች ቻይና ከአለም ጋር በተሻለ ሁኔታ እንድትገናኝ እና አለም ቻይናን ተገቢው ሁኔታ እንዲረዳ ለማድረግ አዳዲስ እና የላቀ አስተዋፅኦ ለማድረግ የታለሙ ናቸው