በቤተ መፃህፍቱ ቻይንኛ፣ እንግሊዘኛ፣ ፈረንሣይኛ፣ ሩሲያኛ፣ ጀርመንኛ፣ ስፓኒሽ፣ ጃፓንኛ እና አረብኛ ጨምሮ በዩኒቨርሲቲያችን የሚሰጡ 101 የቋንቋ ኮርሶችን የሚያጠቃልሉ በ107 ቋንቋዎች የተፃፉ የመፅሃፍት ስብስብ አለው። በድምሩ ወደ 1.6 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰነዶች፣ ከ1.41 ሚሊዮን በላይ የኤሌክትሮኒክስ መጻሕፍት፣ 873 የቻይንኛ እና የውጪ ጋዜጦች እና ወቅታዊ ጽሑፎች፣ ከ10,000 በላይ የሆኑ የተለያዩ የኦዲዮ ቪዥዋል ማቴሪያሎች ሲይዝ ወደ 38,000 የሚጠጉ የቻይንኛ እና የውጭ ቋንቋዎች ሙሉ የኤሌክትሮኒክስ ጆርናሎች፣ 103 የቻይንኛ እና የውጭ ቋንቋ የመረጃ ቋቶች እና 9 በራሱ የተገነቡ ልዩ የመረጃ ቋቶች አሉት። ቤተ መፃህፍቱ ከመነሻው ቋንቋ፣ ሥነ ጽሁፍ እና ባህልን ዋና መሠረት ያደረገ የክምችት ባህሪ ያለው ነው።