እኤአ መጋቢት 6 ቀን 2026፣ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን የቻይና እና የውጭ አገር ሴቶች በተገኙበት በታላቅ ዝግጅት በቤጂንግ ተከብሯል። በሥነ ሥራዓቱ ላይ የቻይና መንግስት ምክር ቤት አባል እና የመላው ቻይና የሴቶች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ቼን ይቺን ንግግር አድርገዋል።
በበዓሉ ላይ ከሚመለከታቸው የማዕከላዊ ኮሚቴ እና ከመንግስት አካላት የተውጣጡ ባለስልጣናት፣ የሴት ተወካዮች እና የብሔራዊ ሕዝባዊ ኮንግረስ እና የቻይና ሕዝባዊ የፖለቲካ ምክክር ኮንፈረንስ አባላት፣ ከሁሉም የኑሮ ደረጃ እና ከሁሉም ብሄረሰቦች የተውጣጡ ታዋቂ ሴት ተወካዮች፣ ከሆንግ ኮንግ እና ማካዎ የተውጣጡ የሴቶች ተወካዮች፣ የቻይና ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ተወካዮች፣ በቻይና የሚገኙ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች እና ከአንድ ሺህ በላይ የቻይና እና የውጭ አገር እንግዶች ተገኝተዋል። ከቤጂንግ ፎሪዬን ስተዲስ ዩኒቨርሲቲ የተውጣጡም አስራ አንድ የውጭ ሀገር ሴት መምህራን በሥነ ሥርዓቱ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘው ተካፋይ ሆነዋል።