ዋናኛ ገጽ (ወደ መነሻ ገጽ ይመለሱ > ዜና

ቤጂንግ ፎሪዬን ስተዲስ ዩኒቨርሲቲ (BFSU) የ2026 የጸደይ ሴሚስተር ዕቅድ

Updated: 2026-03-17

እኤአ የካቲት 28 ቀን 2026 ሁሉም የBFSU አመራሮች በተገኙበት ዩኒቨርሲቲውን የ2026 የጸደይ ሴሚስተር ዕቅድ ለማውጣት በYifu ህንፃ ውስጥ ስብሰባ ካሂዷል። በስብሰባው ላይ የፓርቲው ፀሐፊ ፕሮፌሰር ሊ ሃይ እና የፓርቲው ምክትል ፀሐፊ እና የዩኒቭርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጂያ ዌንጂያን የዩኒቨርሲቲውን አዲሱ ዓመት የተለያዩ ተግባ ዕቅዶች በቅደም ተከተል ዘርዝረዋል።

ፕሮፌሰር ሊ ሃይ ዓለም አቀፍ ትብብርን አስመልከተው ሲናገሩ ዩኒቨርሲቲው እንደ ዓለም አቀፍ ቋንቋዎች፣ ባህሎች እና አስተዳደሮች ባሉ ቁልፍ ዘርፎች ላይ ማተኮር እንዳለበት እና በሩን ለውጭው ዓለም ክፍት ማድረግ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን የመፍጠር ጥረቱን ማስተባበር አለበት ብለዋል። ዩኒቨርሲቲው በተጨማሪም የቻይና-የውጭ ሀገራት የትብብር ትምህርት ፕሮግራሞችን ጥራት እና ቅልጥፍና ለማሻሻል በዓለም ታዋቂ ከሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በከፍተኛ ደረጃ እና በተለያዩ ዘርፎች በንቃት መሳተፍ አለበት። BFSU የኮንፊሽየስ ኢንስቲትዩቶችን ልማት በብቃት በማሳደግ ታዋቂና ገናና ስሙን የጠበቀ የባህል ማስፋፋት ለማሳደግ "የቻይና ድልድይ" እንደተሰኘው ፕሮግራም ባሉ ልዩ የውድድር ፕሮግራሞች ውጤታማ በሆነ መንገድ ያስፈጽማል በማለት አክለዋል፡፡ ፕሮፌሰር ጂያ ዌንጂያን በበኩላቸው BFSU ለአለም አቀፍ ትብብር አዳዲስ አድማሶችን በመክፈት፣ SOAS ከተሰኘው ለንደን ዩኒቨርሲቲ ጋር ያለውን የትምህርት ትብብር ፕሮግራም በተቀላጠፈ ሁኔታ ተግባራዊ ማድረግ ሙሉ በሙሉ ማሳደግ፣ ለአለም አቀፍ የትብብር ትምህርት አዲስ ሞዴል መፍጠር፣ ለኮንፊሺየስ ተቋማት አዲስ መድረክ እና "111 ባለመያዎች ቅጥር መሠረቶች" ለተሰኘው ፕሮጄክት አዲስ መቹ ሁኔታን መፍጠር፣ ጥሩ የረጅም ጊዜ እቅዶችን ማዘጋጀት ተግባራዊ ማድረግ ያሰፈልጋል፡፡ ብሔራዊ ስትራቴጂችን በንቃት ማገልገል፣ ከፍተኛ ጥራት ያለው የትምህርት ትብብር ልማትን ማሳደግ እና "ትምህርት በቻይና" የሚለውን ታዋቂ መለያ ስም እና የአቅም ግንባታ ማራመድ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።