ዋናኛ ገጽ (ወደ መነሻ ገጽ ይመለሱ > ዜና

የአፍሪካ ጥናት ኢንስቲትዩት ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች "የቻይና - ኢትዮጵያ የወዳጅነት ሽልማት" በማሸነፋቻው የምርምር የገንዘብ ድጋፍ አገኙ፡፡

Updated: 2026-01-20

ከቢ ኤፍ ኤስ ዩ የአፍሪካ ጥናት ትምህርት ቤት ባልደረባ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የቻይና እና ኢትዮጵያ የወዳጅነት ሽልማት የምርምር ድጋፎችን አሸነፉ፡

በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 2025/2026 የቻይና እና ኢትዮጵያ ወዳጅነት ሽልማት ያሸነፉ የምርምር ድጋፍ ተሸላሚዎች ዝርዝር በቅርቡ ይፋ አድርጓል። በዚህም ከአፍሪካ ጥናት ትምህርት ቤት የአማርኛ ቋንቋ ባለሙያዎች  ረዳት ፕሮፌሰር ስንቅነሽ አጣለ A Sociocultural Analysis of Chinese–Ethiopian Workplace Communication to Strengthen Bilateral Ties” እንዲሁም ተባባሪ ፕሮፌሰር ሙሉሰው አስራቴ "The Contribution and Potential of Amharic Language Teaching at Beijing Foreign Studies University to Promoting China-Ethiopia Relations." በሚሉ ርዕሶች ያቀረቧቸው የምርምር ፕሮጀክቶቻቸው በተሳካ ሁኔታ በማለፋቸው የምስክር ወረቀትና ለምርምሮቹ የተመደበውን ማበረታቻ ሽልማት አግኝተዋል፡፡

ስንቅነሽ አጣለ (ዶ/ር) 

ሙሉሰው አሥራቴ (ዶ/ር)

በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋራ የሚያካሂዱት "የቻይና-ኢትዮጵያ ወዳጅነት የምርምር ሽልማት" የድጋፍ መርሃ ግብር ዓላማ ኢትዮጵያውያን ምሁራን የሁለቱን ሀገራት የጠበቀ ወዳጅነት የሚመለከቱ ጥራት ያላቸው ምርምሮች እንዲያደርጉ በመደገፍ የሁለትዮሽ ግንኙነቱን የበለጠ ማጠናከር እና አካዳሚክ አለማቀፋዊነትን እና ፈጠራን ማጎልበት ነው።

የአፍሪካ ጥናት ትምህርት ቤት ለበርካታ አመታት "ወዳጅነትን በስኮላርሺፕ ለማሳደግ እና በእውቀት ላይ የተመሠረተ ውይይትን ለማበረታታት" በርካታ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል፡፡ ለዚህም የውጭ ሀገር ባለሙያዎችን በማበረታታት እና በመደገፍ በትምህርት ቤቱ የአካዳሚክ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እና የወዳጅነት አምባሳደርነት ሚናቸውን በመጫወት አዎንታዊ ውጤቶችን እንዲያስመዘግቡ በንቃት በመርዳት ላይ ይገኛል፡፡ ትምህርት ቤቱ ኢትዮጵያዊያን ባልደረቦቻችን ይህንንን ሽልማት በማግኘታቸው የተሰማውን ደስታ ይገልፃል፡፡

ጃንግ ቹንጋይ

አርትዖት፤ ሊ ሆን ፈን

የአፍሪካ ጥናቶች ትምህርት ቤት