ዋናኛ ገጽ (ወደ መነሻ ገጽ ይመለሱ > ዜና

የደቡብ አፍሪካ የስፖርት፣ የኪነጥበብ እና የባህል ሚኒስትር ጌይተን ማኬንዚ ከልዑካቸው ጋር ቤጂንግ ፎሪዬን ስተዲስ ዩኒቨርሲቲን ጎበኙ፡፡

Updated: 2025-12-19

ታህሳስ 3 ቀን፣ ደቡብ አፍሪካ የስፖርት፣ የኪነጥበብ እና የባህል ሚኒስትር ጌይተን ማኬንዚ የሚመራ የልዑካን ቡድን ቤጂንግ ፎሪየን ስተዲስ ዩኒቨርሲቲን (BFSU) ጎብኝቷል። የBFSU ፕሬዝዳንት እና ዩኒቨርሲቲው የኮሚኒስት ፓርቲ ምክትል ፀሐፊ ፕሮፌስር ጂያ ዌንጂያን እና የፓርቲ ኮሚቴው ቋሚ ኮሚቴ አባል እና ምክትል ፕሬዝዳንት ፕሮፌስር ሊዩ ዢንሉ ልዑካኑ ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ ሁለቱ ወገኖች በሰራተኞች ልውውጥ፣ በጋራ ምርምር፣ ክላሲክ ስራዎች በመተርጎም እና የኪነጥበብ ትብብር በመሳሰሉ ዘርፎች ላይ የበለጠ ትብብርን ስለማስፋት ውይይት አድርገዋል።