ህዳር 21 ቀን፣ የ2025ቱ የእስያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ፎረም (AUPF) የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት እና አጠቃላይ ስብሰባ በጓንዡ ተካሂዷል። የፎረሙ ጭብጥ "አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እና ዘርፈ ብዙ ትብብር ፡ በእስያ ከፍተኛ ትምህርት ውስጥ ለጠንካራ እና ሁሉን አቀፍ እድገት አዳዲስ ፈር ቀዳጅ መንገዶችን ዕውን ማድረግ" የሚል ነበር፡፡ የቤጂንግ ፎሪዬን ስተዲስ ዩኒቨርሲቲ የፓርቲ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፀሐፊ ፕሮፌሰር ጂያ ዌንጂያን በፎረሙ ላይ እንዲገኙና ንግግር እንዲያደርጉ በተጋብዙት መሠረት "ዓለምን የሚያገናኝ ድልድይ—የBFSU ብሔራዊ ዓለም አቀፍ የቋንቋ አገልግሎት መድረክ" በሚል ርዕስ ንግግር አድርገዋል።