ህዳር 19 ቀን የትምህርት ሚኒስቴር የፓርቲ ቡድን በቤጂንግ ፎሪዬን ስተዲስ ዩኒቨርሲቲ አስፈላጊ የሹም ሽር ውሳኔዎችን አስተላልፏል። አቶ ሊ ሃይ የቤጂንግ የዩኒቨርሲቲው የፓርቲ ፀሐፊ ሆነው ተሹመዋል። በአንፃሩ ፕሮፌሰር ዋንግ ዲንግዋ ከነበራችው የፓርቲ ፀሐፊነት ተነስተዋል፡፡የፓርቲው ቡድን አባል፣ ምክትል ሚኒስትር እና የትምህርት ሚኒስቴር ዋና ኢንስፔክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ዋንግ ጂያዪ በስብሰባው ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። የትምህርት ሚኒስቴር የሰራተኞች ክፍል ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ገ ዩዋንጂ እና የቤጂንግ የማዘጋጃ ቤት የትምህርት ኮሚቴ ምክትል ፀሐፊ የሆኑት ፕሮፌሰር ዩ ቼንግዌን በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል። ስብሰባውን የመሩት የፓርቲው ምክትል ፀሐፊ እና የቤጂንግ ፎሪየን ስተዲስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የሆኑት ፕሮፌሰር ጂያ ዌንጂያን ናቸው።