ዋናኛ ገጽ (ወደ መነሻ ገጽ ይመለሱ > ዜና

የስፔን ንግሥት ሌቲዚያ ቤጂንግ ፎሪን ስተዲስ ዩኒቨርሲቲን (BFSU) ጎበኙ።

Updated: 2025-11-17

ህዳር 13 ቀን የስፔን ንግሥት ሌቲዚያ ቤጂንግ ፎሪን ስተዲስ ዩኒቨርሲቲን (BFSU) ጎብኝተዋል። በጉበኝቱ ወቅት ዶ/ር ን ዩኩን ቻይና ትምህርት ሚኒስቴር ኮሚኒስት ፓርቲ አመራር ቡድን አባል እና ምክትል ሚኒስትር ፕሮፌሰር ያንግ ዳን ትምህርት ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ትብብርና ግንኙነት መምሪያ ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ዋን ዲንየBFSU የፓርቲ ኮሚቴ ጸሐፊ ፕሮፌሰር ጂያ ዌንጂያን የዩኒቨርሲቲው ፓርቲ ኮሚቴ ምክትል ጸሐፊ እና የBFSU ፕሬዝዳንት እንዲሁም ፕሮፌሰር ዣኦ ጋንግ የዩኒቨርሲቲው የፓርቲ ኮሚቴ ቋሚ ኮሚቴ አባል እና የBFSU ምክትል ፕሬዝዳንት በዝግጅቱ ላይ ተገኝተዋል። በተጨማሪም ከBFSU ስፓኒሽ እና ፖርቱጋል ጥናት ትምህርት ቤት፣ ከBFSU አለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ቤት፣ ከBFSU የትምህርት ትምህርት ቤት እና ከሌሎች የቤጂንግ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ከ300 በላይ መምህራን እና ተማሪዎች በዝግጅቱ ላይ ተሳትፈዋል።

ንግሥት ሌቲዚያ በዝግጅቱ መጀመሪያ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር እና የዩኒቭርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ከሆኑት ዶ/ር ረን ዩኩን ፣ ፕሮፌሰር ያንግ ዳን፣ ፕሮፌሰር ዋን ዲንኋ፣ ፕሮፌሰር ጂያ ዌንጂያን እና ሌሎችም ጋር በመሆን የመታሰቢያ ሰሌዳ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው በ1950ዎቹ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቤጂንግ ፎሪን ስተዲስ ዩኒቨርሲቲ እና ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የስፔንኛ ቋንቋ ኮርሶችን ለማስተማር ለመጡት የስፔን መምህራን ምስጋና እና አክብሮታቸውን ገልጸዋል።

በቤጂንግ ፎሪን ስተዲስ ዩኒቨርሲቲ (BFSU) የስፓንኛ እና የፖርቹጋልኛ ቋንቋዎች ትምህርት ቤት ዲን የሆኑት ቻንግ ፉሊያን በBFSU እና በቻይና በሚገኙ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የስፓንኛ ቋንቋ ትምህርት እና ምርምር እድገትን እና አሁን ያለበትን ደረጃ አስተዋውቀዋል። በተጨማሪም በBFSU የስፓንኛ ቋንቋ ተማሪ የሆነው ማ ኬይንግ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ተማሪው አልቤርቶ በስፓንኛ እና በቻይንኛ ንግግር አድርገዋል ይህም ቻይናዊያን እና ስፔናዊያን ወጣቶች በቋንቋ ትምህርት ላይ ያላቸውን የጋራ መነሳሳትን እና ስሜትን የሚያሳይ ነው

በጉበኝቱ ወቅት ንግሥት ሌቲዚያ BFSU የስፓንኛ ቋንቋን በማስተማር፣ በምርምር እና በአካዳሚክ ግንኙነት ስላስመዘገበው ስኬት በታላቅ ጉጉት ትምህርት ከመቅሰማቸውም በላይ በጉብኝቱ ሥነ ሥራዓት ላይ ከተገኙት መምህራንና ተማሪዎች ጋር ሞቅ ያለና ወዳጅነት የተሞላብት ውይይት አድርገዋል።