የተባበሩት መንግስታት ዩኒቨርሲቲ፣ በቻይና የተባበሩት መንግስታት፣ የቤጂንግ ፎሪየን ስተዲስ ዩኒቨርሲቲ እና የደቡብ አፍሪካው ኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ በጋራ ያዘጋጁት“የመጪው ጊዜ የአተገባበር ስምምነት በዩኒቨርሲቲዎች”በሚል ሃሳብ ላይ የሚያተኩር ውይይት ኦክቶበር 16/ 2025 በቤጂንግ ፎሪየን ስተዲስ ዩኒቨርሲቲ BFSU ተካሄዷል።

በትምህርት ሚኒስቴር የአለም አቀፍ ትብብር እና ግንኙነት ዲፓርትመንት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ሊ ሃይ (Li Hai)፣ የተባበሩት መንግስታት የፖሊሲ ጉዳዮች ምክትል ዋና ፀሀፊ ጋይ ራይደር (Guy Ryder)፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ ስራ አስፈፃሚ ፅህፈት ቤት የመጪው ጊዜ ትግበራ ስምምነት ዳይሬክተር ቴምባ ካውላ (Themba Kaula)፣ በቻይና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስተባባሪ ሲድሃርት ቻተርጄ (Siddharth Chatterjee) እና የቢኤፍኤስዩ የፓርቲ ፀሐፊ ዋንግ ዲንኋ በመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግሮች አድርገዋል።
“የመጪውን ጊዜ ስምምነትን ተግባራዊ ማድረግ እና ዓለም አቀፋዊ አስተዳደርን ማሻሻል” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በዚህ ውይይት ላይ ከተለያዩ አህጉራት የተውጣጡ የዩኒቨርሲቲዎች ተወካዮች፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣናት እና እንደ የትምህርት ሚኒስቴር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያሉ የሚመለከታቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እንዲሁም የመላው ቻይና ወጣቶች ፌዴሬሽን ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል። በስብሰባው በዩኒቨርሲቲዎቹ መካከል ስለሚኖርው "የመጪው ጊዜ የጋራ መግባባትን ለማሳካት የሚያስችል የተግባር እቅድ" በይፋ ተጀምሯል፡፡