በቤጂንግ ፎሪየን ስተዲስ ዩኒቨርሲቲ (BFSU) እና በጀጂያንግ ዓለም አቀፍ ጥናት ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው አምስተኛው ዓለም አቀፍ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲዎች የፕሬዚዳንቶች ፎርም(GAFSU) ጥቅምት 24 ቀን በሀንጆኡ ተካሂዷል።

በውይይት መድረኩ ከ24 የህብረቱ አባል ተቋማት የተውጣጡ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል። ከእነዚህም መካከል የቻይና የአለም አቀፍ ትብብር ማህበር ፕሬዝዳንት እና የቀድሞው የቻይና የትምህርት ሚኒስትር ም/ሚንስትር ሊዩ ሊሚን ፣ የGAFSU ሊቀመንበር፣ የBFSU ፕሬዝዳንት እና የBFSU የኮሚኒስት ፓርቲ ኮሚቴ ምክትል ፀሀፊ የሆኑት ጂያ ወንጂያን፣ የGAFSU ቦርድ አባል እና የጀጂያንግ ዓለም አቀፍ ጥናቶች ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጃንግ ሁዋንጆው እና ሌሎች አመራሮች በፎርሙ ላይ ተገኝተዋል።
"የወደፊት መፍትሄዎች፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ማጎልበት፣ የተቀናጀ ልማት" በሚል መሪ ቃል በ27 አገሮች የሚገኙ፣ ከ60 በላይ ዩኒቨርሲቲዎችና ተቋማት የተውጣጡ ከ170 በላይ ዓለም አቀፍ ባለሙያዎችና ሙሁራን በፎርሙ ላይ ተገኝተዋል። ፎርሙ "በዲጂታል ኢንተለጀንስ ዘመን በቋንቋ ትምህርትና ምርምር ውስጥ የፈጠራ ሥራን በትብብር ለማሳደግ የሚኖረውን ተነሳሽነት" አጉልቶ አሳይቷል።