እ.ኤ.አ. ኦክቶበር 15፣ 2025 የቡልጋሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ኢሊያና ዮቶቫ ቤጂንግ ፎሪየን ስተዲስ ዩኒቨርሲቲን ጎብኝተዋል። የ BFSU ፕሬዝዳንት እና የዩኒቨርሲቲው ፓርቲ ኮሚቴ ምክትል ፀሃፊ ጂያ ዌንጂያን ከዮቶቫ እና ልዑካን ቡድናቸው ጋር ተገናኝተዋል።
 
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ጂያ ዌንጂያን የBFSUን ዓለም አቀፍ ግንኝኙነቶችን፣ የተማሪዎችን ሥልጠና እና የባለብዙ ወገን ዲሲፕሊን ውህደት ልማት መስክ የቅርብ ጊዜ ስኬቶችን አስተዋውቀዋል። ፕሬዘዳንቱ በንግግራቸው BFSU ለቡልጋሪያኛ ቋንቋ ፕሮግራም እና ዲሲፕሊን እድገት ትልቅ ትኩረት እንደሚሰጥ ገልፀው የቡልጋሪያ መንግስት እና በቻይና የሚገኘው የቡልጋሪያ ኤምባሲ ለBFSU የሚያደርጉትን ድጋፍና እገዛ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል። BFSU በሁለቱ ሀገራት ወጣት ሙሁራን መካከል ትብብሮችን እና ግንኙነቶችን በንቃት ለማስተዋወቅ እና የሁለቱን ህዝቦች ወዳጅነት ለማሳደግ የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማድረግ የቋንቋን የድልድይነት ጥቅሞች ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም በትጋት ይሠራል በማለት ነግግራቸውን ደምድመዋል። የቡልጋሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ዮቶቫ በበኩላችው የሰብአዊነት ልማትን አስፈላጊነት አፅንዖት ሰጥተው ወደፊት በሁለቱ ሀገራት ተማሪዎች እና በምሁራን መካከል ተጨማሪ ትብብሮች እና ግንኙነቶችን እንደሚጠናከሩ ያላቸውን ዕምነት ገልፀዋል። የቡልጋሪያ መንግስትም ከBFSU ጋር በመተባበር የሁለቱን ህዝቦች ወዳጅነት በትምህርት ትብብር በኩል ለማጠናከር ፈቃደኛ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ምክትል ፕሬዝዳንት ዮቶቫ ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ጋረ ያደረጉትን ስብሰባ ከጨረሱ በኋላ ለBFSU መምህራን እና ተማሪዎች ንግግር ከማድርጋቸውም በላይ ከታዳሚዎቹ ጋር ውይይት አካሂደዋል።
በዝግጅቱ ላይ ምክትል ፕሬዝዳንቷ በBFSU የቡልጋሪያ ጥናት ማእከል ልዩ ተመራማሪ የሆኑትን ማ ሲፑን የቡልጋሪያን ታሪክ እና ባህል በቻይና እንዲስፋፋ ላደረጉት የላቀ አስተዋፅዖ በማመስገን የቡልጋሪያ ሪፐብሊክ የቅዱስ ሲረል እና የቀዱስ መቶድየስ የመጀመሪያ ደረጃ ሜዳሊያ ሸልመዋቸዋል።