ዋናኛ ገጽ (ወደ መነሻ ገጽ ይመለሱ > ዜና

ቤጂንግ ፎሪዬን ስተዲስ ዩኒቨርሲቲ የ2025 አዲስ ተማሪዎች የአቀባበል ሥነ ሥርዓት አካሄደ።

Updated: 2025-10-17

     ቤጂንግ ፎሪዬን ስተዲስ ዩኒቨርሲቲ ሴፕቴምበር 1 ቀን 2025 የአዲስ ተማሪዎች የቅበላ ሥነ ሥርዓቱን አካሂዷል። በዚህ የትምህርት ዘመን ከ90 የዓለም ሀገራት እና ከተለያዩ የቻይና ክልሎች የተውጣጡ በአጠቃላይ 3,917 አዳዲስ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ተቀላቅለዋል።

BFSU የፓርቲ ኮሚቴ ፀሐፊ ዋንግ ዲንኋ የፓርቲው ኮሚቴ ምክትል ፀሐፊ እና ዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዌንጂያን፣ የፓርቲው ኮሚቴ ምክትል ፀሐፊዎች የሆኑት ጂያ ዴጆንግ እና ዳፐንግየፓርቲው ኮሚቴ የቋሚ ኮሚቴ አባላት እና ምክትል ፕሬዚዳንቶች ዲንግ ሃኦ እና ጃኦ ጋንግበቻይና የጆርጂያ አምባሳደር ባዳ ካላንዳዴዝ እና 2013 BFSU ዓለም አቀፍ ቢዝነስ ትምህርት ቤት የቀድሞ ተማሪ እና ‹‹ ዓለምን ይጎብኙ (出走世界)›› የበጎ ፈቃደኞች የጉዞ መድረክ መስራች ዋንግ ዩሃኦ በአዲስ ተማሪዎች አቀባበል ሥነ ሥርዓ ላይ ተገኝተዋል

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ጂያ ወንጂያን በአዳዲስ ተማሪዎች አቀባበል ሥነሽርዓቱ ላይ ለ2025 አዳዲስ ተማሪዎች እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ልባዊ ምኞታቸውንና ተስፋቸውን የሚገልፅ ሞቅ ያለ ንግግር አድርገዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ላይ አምባሳደር ባዳ ካላንዳ፣ የቀድሞ ተማሪዎች ተወካዮች፣ የመምህራን ተወካዮች፣ እንዲሁም የቅድመ ምረቃ፣ የድህረ ምረቃ እናአለም አቀፍ ተማሪዎች ተወካዮች ንግግር አድርገዋል።

የBFSU የፓርቲ ኮሚቴ ፀሐፊ ዋንግ ዲንጉኋ ለአዲስ ተማሪዎች ተወካዮች የዩኒቨርሲቲውን ባጆች በደረታቸው ላይ ካደረጉላቸው በኋላ የተማሪ መታወቂያ ካርዶችን አሰራጭተዋል።

ቀጥሎም የአዲሶቹ ተማሪዎች ተወካዮች በቦታው ለነበሩት የፋኩልቲዎች ተወካዮች እቅፍ አበባ ካበረከቱ በኋላ አዳዲስ ተማሪዎቹ በተወካያቸው እየተመሩ የአዲስ ገቢ ተማሪዎችን ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲው መዝሙር ከተዘመረ በኋላ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ በደመቀና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።